ንግድ ባንክ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷል

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየከወኑ የሚገኙት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዝመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተቀላቀለበት ዓመት የሊጉን ክብር ያሳካው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቀጣዩ የውድድር ዘመንም ሆነ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ ተሳታፊ በመሆኑ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በአዳማ ከተማ እየከወነ የሚገኝ ሲሆን ውላቸው ተጠናቆ የነበረውን የወሳኝ ተጫዋቾቹን አዲስ ግደይ እና የጋናዊውን ካሌብ አማንኩዋን ውል ማራዘማቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾች ውል ቡድኑ አራዝሟል።

በክለቡ ውላቸው የተራዘመላቸው ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ቡድኑን በመቀላቀል ሁለት ዓመታት ያሳለፈው የግብ ዘቡ ፓላክ ቾል ፣ ሀምበሪቾን በመልቀቅ በቡድኑ ውስጥ የአንድ ዓመት ቆይታ የነበረው ተከላካዩ እንዳለ ዮሐንስ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በክለቡ የሚቆዩ ይሆናል።