ዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸውን መቼ ያደርጋሉ?

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የማጣርያ ጨዋታዎቹን የሚያደርግበት ቀን ታውቋል።


ሞሮኮ ለምታዘጋጀው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በምድብ 8 ከታንዛኒያ፣ ጊኒ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር የተደለደሉት ዋልያዎቹ የማጣርያው ውድድሩ የመጀመርያ ጨዋታ የሚያካሂዱበት ቀን ታውቋል። በዚህ መሰረት ቡድኑ ነሀሴ 27 ከሜዳው ውጭ ታንዛንያን በመግጠም ማጣርያውን የሚጀምር ይሆናል።

ብሄራዊ ቡድኑ በሁለተኛው መርሀ ግብር ጳጉሜ 4 በሜዳው ዴሞክራቲክ ኮንጎን (ጨዋታው በሀገራችን ይደረግ አይደረግ እርግጥ ባይሆንም) በሦስተኛው ደግሞ ከሜዳው ውጭ ጊኒ የሚገጥም ሲሆን የምድቡ አራተኛና አምስተኛው ጨዋታው በሜዳው ከጊኒና ከ ታንዛኒያ የሚያከናውን ይሆናል። ቡድኑ ዴሞክራቲክ ኮንጎን ከሜዳው ውጭ በመግጠም የማጣሪያ ውድድሩን ያገባድዳል።