ድሬዳዋ ከተማ በዝውውር መስኮቱ በንቃት መሳተፉን ቀጥሏል

ብርቱካናማዎቹ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብሰባቸው ሲቀላቅሉ የሁለት ተጫዋቾችን ውል ደግሞ አራዝመዋል።

ከደቂቃዎች በፊት መሐመድኑር ናስርን ከኢትዮጵያ ቡና ፤ አብዱልሰላም የሱፍን ደግሞ ከሀምበርቾ አስፈርመው የግብ ጠባቂያቸውን ዐብዩ ካሣዬ ውል ያራዘሙት ድሬዳዋ ከተማዎች አሁን ደግሞ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለባቸው አምጥተው የሁለት ተጫዋቾችን ውል ማራዘማቸው ታውቋል።


ቡድኑን የተቀላቀሉት አዲስ ከተሾሙት አሰልጣኝ ይታገሡ እንዳለ ጋር በአዳማ ከተማ ቆይታ የነበራቸው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ጀሚል ያዕቆብ እና አማካዩ መስዑድ መሐመድ ሲሆኑ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾች የሆኑት ሄኖክ ሀሰን እና ያሬድ ታደሰ ደግሞ ውላቸው ተራዝሞላቸዋል።