የመስመር ተጫዋቹ የወልዋሎ አዲሱ ፈራሚ ለመሆን ተቃርቧል

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት ወልዋሎዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል።

በትናንትናው ዕለት የሦስት ተጫዋቾች ዝውውር በማገባደድ በክረምቱ ያዘዋወሯቸው ተጫዋቾች ቁጥር ወደ ስምንት ከፍ ያደረጉት ወልዋሎዎች ባለፈው የውድድር ዓመት ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያሳለፈውን የመስመር ተጫዋቹ ጋዲሳ መብራቴ ለማስፈረም ተቃርበዋል። በውድድር ዓመቱ ሰራተኞቹ በሊጉ እንዲተርፉ የጎላ ድርሻ ከተጫወቱ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ይህ ተጫዋች በሀያ ስድስት ጨዋታዎች(1909 ደቂቃዎች’ ) ቡድኑን በማገልገል አምስት ግቦች ማስቆጠር ችሏል።

ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ጨምሮ በደደቢት፣ ኒያላ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ድሬዳዋ ከተማና ወልቂጤ ከተማ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ የቡድኑ ስምንተኛ ፈራሚ ለመሆን ከዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ ለሚመለሱት ወልዋሎዎች ፌርማውን ለማኖር ከጫፍ ደርሷል።