ጦሩ የኋላ ደጀን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

ቡድኑን እያጠናከረ የሚገኘው መቻል ጋናዊውን የተከላካይ መስመር ተጫዋች አስፈርሟል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የዋንጫ ፉክክር ውስጥ የነበረው መቻል በቀጣዩ ዓመት በዚሁ ብርታት ለመዝለቅ ስብስቡን እያጠናከረ የሚገኝ ሲሆን የአሠልጣኙን ውል ካራዘመ በኋላ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በማስፈረም የውድድሩን ጅማሮ በቅድመ ውድድር ዝግጅት እየተጠባበቀ ይገኛል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ጋናዊውን የተከላካይ መስመር ተጫዋች ኤድዊን ፍሪምፖንግ ማንሶን አስፈርሟል።

የቀድሞ የአሳንቴ ኮቶኮ እና ሊብሪቲ ፕሮፌሽናልስ ተጫዋች 2011 የኢትዮጵያን እግርኳስ የተቀላቀለ ሲሆን ያለፉትን ስድስት ዓመታትም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት መልካም የሚባል ግልጋሎት ሰጥቷል። የመሀል ተከላካዩ አሁን ደግሞ 2017 እና 2018 የመቻልን መለያ ለመልበስ ስምምነት ላይ ደርሷል።