ወልዋሎ የመሃል ተከላካዩን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል

ላለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በብርቱካናማዎቹ ቤት ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ቢጫዎቹ ለማምራት ተስማማ።


በርከት ያሉ ዝውውሮች በመፈፀም ቡድናቸውን በማጠናከር ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች ቀደም ብለው ጋዲሳ መብራቴን ለማስፈረም መስማማታቸው ይታወሳል፤ አሁን ደግሞ በብርቱካናማዎቹ ቤት ቆይታ የነበረው የመሃል ተከላካዩ ኢያሱ ለገሰን ለማስፈረም ተስማምተዋል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በድሬዳዋ ከተማ ሲጫወት የቆየው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሃያ ስምንት ጨዋታዎች ተሰልፎ ለ2501′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ይህ ተጫዋች ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ታዳጊ እና ዋናው ቡድን፣ ደደቢት ፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ድሬዳማ ከተማ እና ለኢትዮጵያ ከአስራ ሰባት፣ ከሃያ እና ከሃያ ሦስት ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች መጫወቱ ይታወሳል።


ተጫዋቹ የሕክምና ምርመራውን አጠናቅቆ ወልዋሎን ለመቀላቀል የተስማማ ሲሆን በዛሬው ዕለት በይፋ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።