በመዲናዋ ቅድመ ዝግጅታቸውን የጀመሩት አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ አብረዋቸው የሚሰሩ የቡድን አባላትን በአዲስ መልክ አዋቅረዋል።
ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ለሁለት ተከታታይ ዓመታት አብሮ ለመዝለቅ ፊርማቸውን በማኖር ለ2017 የውድድር ዘመን ግጅታቸውን የጀመሩት አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ አጠገባቸው በመሆን የሚረዷቸውን የቡድን አባላቶችን ለክለቡ አሳውቀዋል።
በዚህም መሠረት በምክትል አሰልጣኝነት ቦታን ደጉ ዱባሞን ሲያደርጉ በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ውብሸትን ደሳለኝን አድርጓል።
አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ካሳለፈ በኋላ በመተሀራ እና አካባቢዋ በርካታ ተጫዋቾችን በማሰልጠን የአሰልጣኝነት ህይወቱን የጀመረ ሲሆን መተሀራ ቡድንን በማሰልጠን በአዳማ ከተማ ረዳት እንዲሁም ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኖ በማገልገል ወደ ሀምበሪቾ በማምራት ቡድኑን ከከፍተኛ ሊግ ወደ በፕሪሚየር ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ቡድኑን በሊጉ ለወራት መሳልጠናቸው ይታወቃል።
የግብጠባቂ አሰልጣኝ የሆነው ውብሸት ደሳለኝ
በክለብ ደረጃ ለብርሃንና ሰላም፣ ለኒያላ፣ ለመከላከያ፣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለኢትዮጵያ መድን፣ ለሰበታ ከተማና ለአዲስ አበባ ከነማ ተጫውቶ አሳልፏል። በብሄራዊ ቡድን ተጨዋችነት ደግሞ ከወጣት ቡድን እስከ ዋናው ቡድን በመጫወት ይታወቃል። ወደ ስልጠናው አለም ቀተቀላቀለ በኋላ በክለብ ደረጃ ኢትዮጵያ ቡና እና በቅዱስ ጊዮርጊስ በብሔራዊ ቡደን በሴቶች እንዲሁም የዋሊያዎቹ ግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆኖ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል።