ዋልያዎቹ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ያላቸውን ጨዋታ ዳሬሰላም ላይ ያደርጋሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው ያደርግ የነበረውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን በታንዛኒያ ያደርጋል።


ሞሮኮ ለምታዘጋጀው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 8 ከታንዛኒያ፣ ጊኒ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር የተደለደሉት ዋልያዎቹ የማጣሪያ ውድድሩ የመጀመሪያዎቹን ጨዋታዎች የሚያካሂዱበት ቀን የታወቀ ሲሆን በዚህ መሰረት ቡድኑ ነሐሴ 29 ከሜዳው ውጭ ታንዛንያን በመግጠም ማጣሪያውን የሚጀምሩ ይሆናል።

ብሔራዊ ቡድኑ በሁለተኛው መርሐግብር ጳጉሜ 4 በሜዳው ዴሞክራቲክ ኮንጎን የሚያስተናግድ ቢሆንም ሀገራችን ውስጥ የካፍን መስፈርት የሚያሟላ ስታዲየም ባለመኖሩ በድጋሚ ከሀገር በመውጣት የመጀመሪያ ጨዋታውን በሚያደርግበት በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዳሬሰላም በሚገኘው ዳሬሰላም ብሔራዊ ስታዲየም እንደሚያደርግ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።