አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ታንዛኒያ ላይ ለሚያደርጋቸው ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጓል።

ሞሮኮ ለምታዘጋጀው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 8 ከታንዛኒያ፣ ጊኒ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር የተደለደሉት ዋልያዎቹ የማጣሪያው ውድድሩ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን የሚያካሂዱበትን ቀን እና ቦታ ከሰዓታት በፊት አስነብበናችሁ ነበር። በዚህ መሰረት ነሐሴ 29/2016 ኢትዮጵያ ወደ ታንዛኒያ ዳሬሰላም አቅንታ የታንዛኒያን ብሔራዊ ቡድን ስትገጥም ጳጉሜ 4/2016 ደግሞ ዲሞክራቲክ ኮንጎን በሜዳዋ ለማስተናገድ መስፈርት የሚያሟላ ሜዳ ባለመያዟ እዛው ታንዛኒያ ላይ ሁለተኛ ጨዋታዋን ታደርጋለች። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የሆኑት ገብረመድኅን ኃይሌም ለሁለቱ ጨዋታዎች ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ 28 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል።

ግብ ጠባቂዎች

ሰዒድ ሀብታሙ – ሀዋሳ ከተማ
አቡበከር ኑራ – ኢትዮጵያ መድን
ፍሬው ጌታሁን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ተከላካዮች

ብርሃኑ በቀለ – ሲዳማ ቡና
ሱሌይማን ሀሚድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ያሬድ ካሳዬ – ኢትዮጵያ መድን
ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ያሬድ ባየህ – ሲዳማ ቡና
ሚሊዮን ሰለሞን – ኢትዮጵያ መድን
ፈቱዲን ጀማል – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፍሬዘር ካሳ – ባህር ዳር ከተማ
አማኑኤል ተርፉ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም – ፋሲል ከነማ
አብነት ደምሴ – ወላይታ ድቻ
በረከት ወልዴ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ወገኔ ገዛኸኝ – ኢትዮጵያ መድን
አብዱልከሪም ወርቁ – መቻል
ቢኒያም በላይ – ሀዋሳ ከተማ
ቢኒያም ዐይተን – አዳማ ከተማ
ሱራፌል ዳኛቸው – ሎውዶን ዩናይትድ

አጥቂዎች

ከነዓን ማርክነህ – መቻል
ቸርነት ጉግሳ – ባህር ዳር ከተማ
ተመስገን ብርሃኑ – ሀዲያ ሆሳዕና
ቢኒያም ፍቅሬ – ወላይታ ድቻ
ምንይሉ ወንድሙ – መቻል
አቤል ያለው – ዜድ
መስፍን ታፈሰ – ሲዳማ ቡና
አቡበከር ናስር – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች እሁድ ነሐሴ 12 በአዳማ ከተማ በመሰባሰብ ዝግጅት እንደሚጀምሩ ተገልጿል።