ኢትዮጵያን የሚወክሉ የጨዋታ አመራሮች ታውቀዋል

የሴካፋ ሀገራት የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር ከኢትዮጵያ የሚወከሉት የጨዋታ አመራሮች ታውቀዋል።


በሀገራችን ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የዘንድሮው የሴካፋ ሀገራት የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በይፋ የሚጀመር ይሆናል። በሁለት ምድብ ተከፍሎ ስምንት ክለቦች በሚሳተፉበት በዚህ ውድድር ኢትዮጵያን የሚክሉ የጨዋታ አመራሮች ተለይተው ታውቀዋል።

በዚህም መሠረት ኢንተርናሽናል አልቢትር ሲሳይ ራያ እና ማርታ መለሰ በዋና ዳኝነት ፣ ኢንተርናሽናል አልቢትር ወጋየሁ ዘውዱ እና ይልፋሸዋ አየለ በረዳት ዳኝነት ሲመደቡ የጨዋታ ኮሚሽነር በመሆን ሳራ ሰኢድ፣ በአሰሰርነት ሊዲያ ታፈሰ እንዲሁም የካፍ አልቢትር ኮሚቴ አባል የሆነችው ተስፋነሽ ወረታ በዳኞች ኮሚቴነት በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል እንደሚሳተፉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።