የካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር አንድ ቡድን ራሱን አግሏል

ነገ በይፋ በሚጀምረው የካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር አንድ ቡድን እራሱን ማግለሉ ታውቋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ በይፋ በሚጀምረው የካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር አብዛኛው ቡድኖች ወደ መዲናዋ እየገቡ እንደሆነ እና የዛንዚባሩ ዋሪየር ኩዊንስ ነገ የመክፈቻ ጨዋታውን ከኬንያ ፖሊስ ጋር ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ቡድኑ እስካሁን አዲስ አበባ አለመግባቱን አስቀድመን መዘገባችን ይታወቃል።

ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ ደግሞ የዛንዚባሩ ዋሪየር ኩዊንስ ከውድድሩ ውጭ መሆኑን ተረጋግጧል። ቡድኑ ከውድድሩ ራሱን ያገለለበት ምክንያት በግልፅ የታወቀ ነገር እንደሌለ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ይህን ተከትሎ ከነገው የመክፈቻ ጨዋታ ውጭ መሆኑ ሲታወቅ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ አዲስ የመርሐ-ግብር ማሻሻያ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።