አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ ተከላካይ አስፈርሟል

በመቻል የአንድ ዓመት ቆይታ የነበረው ጋናዊ ተከላካይ ወደ አዞዎቹ ቤት አምርቷል።

በአሰልጣኝ በረከት ደሙ እየተመሩ በክለቡ መቀመጫ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ማድረግን የቀጠሉት አርባምንጭ ከተማዎች በዝውውር መስኮቱ ይሁን እንዳሻው ፣ ካሌብ በየነ ፣ ሙሉጌታ ካሳሁን እና ፋሪስ ዓለዊን ከፕሪምየር ሊጉ ሲያስፈርሙ ትላንት ደግሞ ከባህር ማዶ ኢድሪሳ ኦጎጆ የተሰኘን ቶጓዊ ግብ ጠባቂ ማስፈረማቸው ይታወሳል።

ትላንት ማምሻውን ደግሞ ጋናዊውን ተከላካይ ስቴፈን ባዱ አኖርኬን የግላቸው አድርገዋል ፤ ተጫዋቹ በሀገሩ ክለቦች ቢ ኤ ዩናይትድ ፣ አዱዋና ስታርስ እና በረኩም ቼልስ የተጫወተ ሲሆን በኦማን ሊግ ለሚሳተፈው ሶሀር እንዲሁም በኩዌት ሊግ ለሚገኘው አል-ታዳሞን ግልጋሎት ሰጥቷል። በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የተዋወቀው ስቴፈን በመቻል ቤት ጥሩ የሚባል ጊዜን ካሳለፈ በኃላ የተከላካዩ ቀጣይ መዳረሻ አርባምንጭ ሆኗል።