የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ አንድ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኬኒያ ፖሊስ ቡሌትን ሁለት ለአንድ አሸንፎ ምድቡን በበላይነት ካጠናቀቀበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች የሰጡት አስተያየት።
አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ስለ ጨዋታው
ለአራተኛ ተከታታይ ዓመት በተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች አሸንፈናል፤ ይሄ ደግሞ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ዛሬ የነበረው የሜዳው ሁኔታ አስቸግሮናል፤ ቡድናችን በተወሰነ መልኩ በፈለግነው መንገድ እንዳይንቀሳቀስ አድርጎታል።
ውድድሩ በኢትዮጵያ እንደመዘጋጀቱ በዚህ ሰዓት በልበ ሙሉነት ስለ ዋንጫ ማሰብ ጀምራችኋል ?
“ከዚህ በፊት በሁለት አጋጣሚዎች በመለያ ምት ነው ዋንጫ ያጣነው አሁን ደግሞ ተጫዋቾቼ ወጣቶች ናቸው፤ በቡድኑ ዋንጫ የማንሳት ፍላጎት ነው ያለው።”
ምክትል አሰልጣኝ ሑሴን ሐቢብ- የኬኒያ ፖሊስ ቡሌትን
ስለ ጨዋታው
“በጣም ከባድ ጨዋታ ነበር ፤ ብዙ ሩጫዎች የነበሩበት አድካሚ የነበረ ጨዋታ ነበር።ሜዳው በራሱ በጣም ፈታኝ ነበር ። እነሱ በታክቲኩ ረገድ እና የቡድን ስራ ላይ ጥሩ ነበሩ።”
ቡድኑ ወደ ቀጣይ ዙር ስላለበት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ?
“የነበሩብን ክፍተቶች በማየት ለቀጣይ ጨዋታ እንዘጋጃለን። ቀጣይ አሁን ካሳየነው ብቃት በተሻለ ሆነን እናቀርባለን።”
ስለ ቀጣይ ተጋጣሚያቸው ሲምባ
“ወሳኙ ነገር የታዩብን ክፍተቶች በልምምድ ሜዳ አስተካክለን በቀጣይ ጨዋታዎች በተለየ መንገድ መቅረብ ነው፤ አሁን ማለት የምችለው ይሄ ነው።”