አቤል ያለው ብሔራዊ ቡድኑን የመቀላቀሉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል

ለግብፁ ክለብ ዜድ እየተጫወተ የሚገኘው አቤል ያለው ብሔራዊ ቡድኑን የመቀላቀሉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ላለባት ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በግብፅ ሊግ እየተጫወተ ለሚገኘው አጥቂው አቤል ያለው ጥሪ ማድረጋቸውን ይታወቃል።


ከክለቡ ጋር ግብፅ የሚገኘው አቤል ያለው ባጋጠመው መጠነኛ ህመም የተነሳ ብሔራዊ ቡድኑን ሊቀላቀል እንደማይችል ተሰምቷል ፤ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ለቡድኑ ግልጋሎት ያልሰጠው አቤል አሁን ላይ ከጉዳቱ ለማገገም የህክምና ክትትል እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ከህመሙ ሙሉ ለሙሉ ለመዳን የሁለት ሳምንት ጊዜ የሚወስድበት መሆኑን ሰምተናል።

ይህን ተከትሎ አቤል ለዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታ የመድረሱ ነገር አጣራጣሪ በመሆኑ ከቡድኑ ስብስብ ውጭ ሊደረግ እንደሚችል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።