ሲዳማ ቡና ዕንስት ሥራ አስኪያጅ ሾሟል

በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የሚመራው ሲዳማ ቡና በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያዋን ሴት ሥራ አስኪያጅ ሾሟል።


ለ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን የልምምድ መርሐግብሩን በሀዋሳ ከተማ እየከወነ የሚገኘው እና በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወሳኝ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ክለብ ሲዳማ ቡና ከቀድሞው ሥራ አስኪያጁ አቡሽ አሰፋ ጋር ከወራቶች በፊት መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ክለቡ በቦታው ሴት ሥራ አስኪያጅ በዛሬው ዕለት በሌዊ ሪዞርት ማምሻውን በነበረ የእራት ፕሮግራም መሾሙን አሳውቋል።

ወ/ሮ ከነዓን በለጠ ደግሞ አዲሷ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ ሆና የተሾመችዋ ዕንስት ሆናለች። በሳይካትሪስት ሙያ ላይ ተሰማርታ “ዘፀአት” የተሰኘ የሕክምና እና የምክር አገልግሎት ተቋም ባለቤት የሆነችው እና የአዕምሮ ጤና ላይ ስትሠራ የነበረችው ዕንስት ቀጣዩዋ የሲዳማ ቡና ሥራ አስኪያጅ መሆኗ ተረጋግጧል።