አሠልጣኝ ገብረመድህን ሁለቱ ቡድናቸውን እርስ በርስ ሊያጋጥሙ ነው

ዋልያዎቹ ከጥቂት ቀናት በኋላ ላለባቸው ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ለመዘጋጀት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው።


በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከታንዛኒያ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ በአምስት ቀን ልዩነት ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ዋልያዎቹ በሳምንቱ መጨረሻ ቀን ከሀገር ውስጥ ክለብ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊያደርጉ እንደሆነ ሶከር ኢትዮጵያ ከመረጃ ምንጮቿ አረጋግጣለች።

የፊታችን እሁድ ነሐሴ 19 ቀን በዘጠኝ ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ እንደሚካሄድ ቀጠሮ በተያዘለት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር እንደሚጫወት ሲታወቅ ለጨዋታው አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ብሔራዊ ቡድናችን የመጀመርያ ጨዋታውን ከታንዛንያ ጋር ነሐሴ 29 ቀን ፣ ሁለተኛ ጨዋታውን ደግሞ ጳጉሜ 4 ቀን ከኮንጎ ዲ.ሪ ጋር በዳሬ ሰላም ብሔራዊ ስታዲየም የሚያደርግ ይሆናል።