ዛሬ አመሻሽ ሞሮኮ ላይ የሚደረግ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ መርሀግብር በአራት የሀገራችን ዳኞች ይመራል።
የ2024/25 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ መደረግ የጀመሩ ሲሆን የመልስ መርሀግብሮችም ከዛሬ ጀምሮ እየተደረጉ ይገኛል። በዛሬው ዕለት 10 ሰዓት ላይ የሞሮኮው አንጋፋ ክለብ ራጃ ካዛብላንካ ከ ኒጀሩ ኤ ኤስ ኤን ኤን የሚያደርጉትን መርሀግብር አራት አለም አቀፍ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች እንዲመሩት መመረጣቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
በመሐል ዳኝነት ዶ/ር ኢንተርናሽናል ዳኛ ሀይለየሱስ ባዘዘው ረዳት በመሆን ደግሞ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኞቹ ተመስገን ሳሙኤል እና ይበቃል ደሳለኝ ፣ ኤፍሬም ደበሌ በበኩሉ በመድረኩ የመጀመሪያ ጨዋታውን አራተኛ ዳኛ ሆኖ ተመድቦበታል።
