የዋልያዎቹን ስብስብ አንድ ተጫዋች ተቀላቅሏል

ዛሬ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር በሚያደርገው የዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ አንድ ተጫዋች መቀላቀሉ ታውቋል።

በቀጣይ ሳምንት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ጥሪ አድርገውለት የነበረው ሱራፊል ዳኛቸው ምንም እንኳን በሀገር ቤት የሚገኝ ቢሆንም ለክለቡ ሎውዶን ዩናይትድ ብሔራዊ ቡድን መጠራቱን እስኪያሳውቅ ድረስ ብሔራዊ ቡድኑን ሳይቀላቀል መቅረቱን ከዚህ ቀደም መዘገባችን አይዘነጋም።

አሁን ባገኘነው መረጃ ሱራፌል ብሔራዊ ቡድኑ ባረፈበት በአዳማ ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል የገባ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ በሚካሄደው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ላይ እንደሚታደም እና ከነገ ጀምሮ ወደ ልምምድ እንደሚገባ ሰምተናል።