ዋልያዎቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን ድል አድርገዋል

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ከሁለቱ ቡድናቸው ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በዋልያዎቹ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ከታንዛኒያ እና ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ነሐሴ 29 እና ጳጉሜ 4 ቀን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዳሬ ሰላም ላይ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ዝግጅታቸውን ከጀመሩ ሰባተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል። ዋልያዎቹ ወደ ስፍራው ከማቅናታቸው አስቀድሞ ዛሬ በአዳማ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በመጀመርያው አጋማሽ ቡድናቸው ግብጠባቂ አቡበከር ኑራ ተከላካይ- ብርሀኑ በቀለ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ ያሬድ ባዬ ፣ ያሬድ ካሳይ አማካይ- አብነት ደምሴ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ቢንያም በላይ አጥቂ – ቸርነት ጉጉሳ፣ ከንዓን ማርክነህ እና ቢንያም ፍቅሬ ሲጠቀሙ በ22ኛው ደቂቃ ቸርነት ጉግሳ በአስቆጠረው ጎል አጋማሹ ተጠናቋል።

ከዕረፍት መልስ የቀኝ መስመር ተከላካይ ብርሀኑ በቀለን ብቻ በማስቀረት ግብጠባቂ ሰኢድ ሀብታሙ ተከላካይ – ረመዳን የሱፍ፣ ፍሬዘር ካሳ፣ አማኑኤል ተርፉ፣ ብርሀኑ በቀለ አማካይ- በረከት ወልዴ፣ ወገኔ ገዛኸኝ፣ አብዱልከሪም ወርቁ አጥቂ- መስፍን ታፈሰ፣ ቢንያም አይተን፣ ምንይሉ ወንድሙ ይዘው የገቡት አሰልጣኙ በዚህኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ምንም ጎል ሳይቆጠር 0ለ0 ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 23 ተጫዋቾችን በመያዝ ነሐሴ 27 ቀን ወደ ዳሬ ሰላም የሚያቀና ይሆናል።