በቀጣይ ሳምንት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምትገጥመው ታንዛንያ ስብስቧን ይፋ አደረገች።
በ2025 ሞሮኮ ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከኢትዮጵያ፣ ጊኒ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ የተደለደለችው ታንዛንያ ኢትዮጵያ እና ጊኒ የሚገጥመው ስብስቧን ይፋ አድርጋለች። ነሐሴ 29 በሜዳቸው ዋልያዎቹን በማስተናገድ የማጣርያ ውድድራቸውን የሚጀምሩት አሰልጣኝ ሐሚድ ሱሌይማን በአመዛኙ ከሦስቱ የሀገሪቱ ታላላቅ ክለቦች የተውጣጣ ስብስብ ይፋ አድርገዋል፤ በዚ መሰረት ያንግ አፍሪካንስ 7 ፣ አዛም 5 ሲምባ ደግሞ ሦስት ተጫዋቾች በማስመረጥ ቅድምያ ይዘዋል።
አሰልጣኙ ቀደም ብሎ በፍቃዱ ከብሄራዊ ቡድኑ ያገለለው በግሪኩ ፓኦክ ሶላንኪ የሚጫወተው የቀድሞ የአስቶንቪላ አጥቂ ምብዋና ሳማታ በስብስባቸው ውስጥ ባያካትቱም በቱርኩ ጎዝቴፔ የሚጫወተው የግራ መስመር ተከላካዩ ኖቫቱስ ሚሮሺ እና በአሜሪካው ቫንኮቨር ዋይትካፕስ የሚጫወተው አጥቂው ሲፕርያን ካችዌለ አካተዋል።