ባህር ዳር ከተማ የቀድሞ አማካዩን አስፈርሟል

የጣና ሞገዶቹ የቀድሞው ተጫዋቻቸውን ሲያስፈርሙ የአማካያቸውን ውል ደግሞ አድሰዋል።

በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው መሪነት በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ባህርዳር ከተማዎች በዝውውር ገበያው ከዚህ ቀደም በቡድናቸው ውስጥ የነበሩ የቀድሞ ተጫዋቾቻቸውን ማስፈረማቸውን ቀጥለውበታል።

ወደ ቀድሞ ቡድኑ የተመለሰው ሌላኛዌ ተጫዋች ደግሞ
አማካዩ ዳንኤል ሐይሉ ሆኗል ፤ ከባህር ዳር የታችኛው ቡድን መነሻውን ካደረገ በኋላ በመቀጠል ለሰበታ ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና እንዲሁም ያለፈውን የውድር ዘመን ደግሞ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በከፍተኛ ሊጉ ቆይታን ካደረገ በኃላ ወደ ቀድሞ ቡድኑ የሚመልሰውን ዝውውር ፈፅሟል።

በሌላ ዜና በቡድኑ ውስጥ ረጅም ጊዜን ያሳለፈው የተከላካይ አማካዩ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ ለአንድ ተጨማሪ ዓመት በባህር ዳር የሚያቆየውን የውል ማራዘሚያ ፈፅሟል።