ከዋልያዎቹ ስብስብ ጋር አንድ ተጫዋች አይገኝም

የኢትዮጵያ ብሔራዊው ቡድን ዛሬ የመጨረሻውን ልምምድ ሲሰራ አንድ ተጫዋች ከቡድኑ ጋር እንደማይገኝ ታውቋል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እየተመሩ ለአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅታቸውን እየሰሩ ቆዮት ዋልያዎቹ ትናት በአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዳቸውን የሰሩ ሲሆን ዛሬም በተመሳሳይ አዲስ አበባ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምምዳቸውን እንደሚሰሩ ይጠበቃል። ታዲያ በዚህ ሰዐት የቡድኑ አባል የሆነ አንድ ተጫዋች ከቡድኑ ጋር እንደማይገኝ እና ከሆቴል እንደወጣ ሰምተናል።

ከቡድኑ ጋር የማይገኘው ተጫዋች የፈረሰኞቹ ተከላካይ አማኑኤል ተርፉ እንደሆነ አውቀናል። አማኑኤል ከቡድኑ ጋር የማይገኘው በምን ምክንያት እንደሆነ ለጊዜው ባናቅም ለአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ አሳውቆ ትናት ማምሻውን ከሆቴል እንደወጣ አረጋግጠናል።

በዚህ መነሻነት ትናት የዋልያዎቹ አለቃ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው ሁለት ተጫዋቾች እንደሚቀነሱ በተናገሩት መሰረት አንዱ ተጫዋች አማኑኤል ተርፉ መሆኑ እርግጥ ሆኗል። ዛሬ ከሰዓታት በኋላ ከሚሰሩት የመጨረሻ ልምምድ በኋላ የሚቀነሰው አንድ ተጫዋች ማን እንደሆነ የሚጠበቅ ይሆናል።