ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ወደ ዳሬ ሰላም የሚያቀኑት የመጨረሻዎቹ ተጫዋቾች ሲታወቁ አንድ ተጫዋች መቀነሱ እርግጥ ሆኗል።
ከፊቱ ላሉበት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ያለፉትን አስራ አምስት ቀናት በአዳማ ከተማ እና በአዲስ አበባ ሲዘጋጅ የቆየው ብሔራዊ ቡድናችን በአዲስ አበባ ስታዲየም ዛሬ ረፋድ ላይ የመጨረሻ ልምምዱን ሠርቶ አጠናቋል። ነገ ወደ ስፍራው ከሚያቀናው የቡድኑ ስብስብ ውስጥ አስቀድመን ባጋራናችሁ መረጃ መሰረት ተከላካዩ አማኑኤል ተርፉ ከብሔራዊ ቡድኑ ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።
ሶከር ኢትዮጵያ አሁን እንደደረሳት መረጃ ከሆነ ከብሔራዊ ቡድኑ ውጭ የሆነውን ሁለተኛውን ተጫዋች ለማወቅ ችላለች። ከስብስቡ ውጭ የሆነው የመቻሉ አማካይ አብዱልከሪም ወርቁ መሆኑ ታውቋል።
በዚህም መሠረት ወደ ዳሬ ሰላም የሚያቀኑት የቡድኑ አባላት ግብጠባቂ – ሰዒድ ሀብታሙ፣ ፍሬው ጌታሁን፣ አቡበከር ኑራ
ተከላካይ – ብርሃኑ በቀለ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ ያሬድ ባየህ፣ ፍሬዘር ካሳ፣ ፈቱዲን ጀማል፣ ያሬድ ካሳዬ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ሱሌይማን ሀሚድ
አማካይ -ጋቶች ፓኖም፣ አብነት ደምሴ፣ ወገኔ ገዛኸኝ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በረከት ወልዴ፣ ቢኒያም በላይ
አጥቂ -ከነዓን ማርክነህ፣ ምንይሉ ወንድሙ ፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ቢንያም ፍቅሬ፣ ቢኒያም ዐይተን እና አዲስ ግደይን በመያዝ ሰኞ ወደ ዳሬ ሰላም የሚያቀኑ ይሆናል።
ብሔራዊ ቡድናችን የመጀመርያ ጨዋታውን ከታንዛንያ ጋር ነሐሴ 29 ቀን ፣ ሁለተኛ ጨዋታውን ደግሞ ጳጉሜ 4 ቀን ከኮንጎ ዲ.ሪ ጋር በዳሬ ሰላም ብሔራዊ ስታዲየም የሚያደርግ ይሆናል።