የመዲናዋ የሲቲ ካፕ ውድድር ይደረጋል

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ከሰዓት በሚካሄድ አንድ የመክፈቻ ጨዋታዎች እንደሚካሄድ ታውቋል።

ኢትዮጵያ ቡና እራሱን ከውድድር ውጭ ማድረጉ እና ውድድሩ በዝግ መካሄዱን ተከትሎ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ ሁኔታ ውስጥ የገባው አስራ ስምንተኛው የአዲስ አበበ ከተማ ዋንጫ ዛሬ በይፋ እንደሚጀመር ታውቋል።

ሰምንት ሰዓት ኢትዮጵያ መድን ከ ፋሲል ከነማ ጋር በሚካሄደው ጨዋታ ውድድሩ የሚከፈት ሲሆን በኢትዮጵያ ቡና ምትክ አንድ ቡድን ለመተካት አወዳዳሪው አካል ጥረት እያደረገ መሆኑን ሰምተናል።

ጥረቱ የሚሳካ ከሆነ በቀጣይ በሚካሄዱ ጨዋታዎች ዙርያ አዲስ መርሐ-ግብር እንደሚወጣ ይጠበቃል።