ወልቂጤ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሾሟል

አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ ሶሬሳ ካሚል ረዳታቸውን አሳውቀዋል።

ለ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ዝግጅታቸውን በሀዋሳ ከተማ እየከወኑ የሚገኙኝት ወልቂጤ ከተማዎች በአዲሱ አሰልጣኝ ሶሬሳ ካሚል ምርጫ የቡድኑ ረዳት አሰልጣኝ ታውቋል።

የቡድኑ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን የተሾሙት አይቼው አባይ ናቸው። በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት ሲያገለግሉ የሚታወቁት አሰልጣኙ በዩኒቨርስቲው የሴት እና የወንድ ቡድኖችንም ጭምር ማሰልጠን ችለዋል። በተጨማሪነት የአርባምንጭ ከተማ ወጣት ቡድንን እንዲሁም በአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የቴክኒክ ሀላፊ እና ረዳት አሰልጣኝ ሆነው ማገልገል የቻሉ ሲሆን በቀጣይም ወደ ወልቂጤ በማምራት በረዳት አሰልጣኝነት የሚያገለግሉ ይሆናል።

እስከ አሁን በፌዴሬሽኑ በተጣለበት በርካታ ዕገዳዎች የተጫዋቾችን ውል ማፀደቅ ያልቻለው ቡድኑ ከግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ቢኒያም ሀብታሙ (ኦሼ) ጋር የሚቀጥልም ይሆናል።