የታንዛኒያው አሠልጣኝ ከጨዋታው በኋላ ምን አሉ?

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያለ ግብ የተለያየውን የታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን የሚመሩት አሠልጣኝ ሄምድ ሱሌይማን ዓሊ ከጨዋታው በኋላ የሰጡትን አጠር ያለ ሀሳብ ይዘን ቀርበናል።

ስለጨዋታው…

ጨዋታው ጥሩ ነበር። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ቡድን ነው። ይሄንንም እናውቃለን። ሁሌ ከኢትዮጵያ ጋር ስንጫወት ጨዋታው ጠንካራ ነው የሚሆነው። ጨዋታውን ለመቆጣጠር በራሳቸው ፍልስፍና ነው የሚጫወቱት። እንደ ቡድን ጥሩ ቅርፅ ሰጥተው ነው የሚጫወቱት። በመጀመሪያው አጋማሽ በመጥፎ ሁኔታ ነው ጨዋታውን የከወነው። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻልን ነበርን። ቦታ ለመፍጠር ስንጥር ነበር። በተለይ በመጨረሻዎቹ 20 እና 25 ደቂቃዎች የተሻለ ለመጫወት ሞክረናል። የግብ ማግባት ዕድሎችንም መፍጠር ችለን ነበር ፤ ግን እነዛን ዕድሎች መጠቀም አልቻልንም። ቀጣዩ የምድብ ጨዋታችን የተሻለ እንደሚሆን አስባለው።