ከ17 ዓመት በታች የክለቦች እና ክልሎች ሻምፒዮና የሚደረግበት ቦታ እና ቀን ታውቋል

ክለቦችን እና ክልሎችን የሚያሳትፈው ከ17 ዓመት በታች ሻምፒዮና የሚዘጋጅበት ከተማ እና የሚጀመርበት ወቅት ይፋ ተደርጓል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ይባል የነበረው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አስተናጋጅነት የሚደረገው ውድድር ላለፉት ሦስት ዓመታት የስም ለውጥ በማድረግ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የክለቦች እና ክልሎች ሻምፒዮና በሚል እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወሳል።

በያዝነው ወር ላይ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የ2016 ውድድር ሽግሽግ ተደርጎበቶ መስከረም ወር 2017 ላይ እንዲደረግ ሲወሰን ውድድሩም በሀዋሳ ከተማ ከመስከረም 4 አንስቶ የሚደረግ ይሆናል።


ከውድድሩ ጅማሮ አንድ ቀን አስቀድሞ ደግሞ የዕጣ ማውጣት እና የቅድመ ስብስባ መርሀግብር እንደሚኖርም ጭምር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፤ ከቀናት በፊት በተመሳሳይ በሀዋሳ ከ17 ዓመት በታች የፓይለት ፕሮጀክት ውድድር በወንዶች ሲዳማ ክልል በሴቶች አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ባለ ድል መሆናቸው ይታወሳል።