ሲዳማ ቡና አራት ተጫዋቾችን ከተስፋ ቡድኑ አሳድጓል

በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎን እያደረጉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ተስፋ ቡድናቸው በማዞር አራት ተጫዋቾችን ከተስፋ ቡድናቸው አሳድገዋል

በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው መሪነት በክረምቱ የዝወውር መስኮት አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ቡድናቸው መቀላቀል የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች መቀመጫቸውን ሀዋሳ በማድረግ ለመጪው ውድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከተስፋ ቡድናቸው አራት ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድገዋል።

ወደ ዋናው ቡድን ያደጉት ተጫዋቾች አንድ ግብ ጠባቂው ስዩም ሌዳሞ ፣ የመስመር ተከላካዩ አስቻለው ሙሴ ፣ የመሀል ተከላካዩ መላኩ አሰፋው እና አጥቂው ኢያሱ ሮንዳ መሆናቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።