የጣና ሞገዶቹ አንድ አማካይ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል

በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ አማካይ ለማስፈረም ተስማምቷል።

ለቀጣይ ውድድር ዘመን ራሳቸውን ለማጠናከር በዝውውሩ ላይ ተሳትፎ ያደረጉት ባህር ዳር ከተማዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ እያደረጉ ሲገኝ አሁን ደግሞ አንድ በተከላካይ አማካይ እና በአማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወት ተጫዋች ለማስፈረም መቃረባቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ለባህር ዳር ለመጫወት የተስማማው ዳዊት ደግአረገ ሲሆን የእግርኳስ ሕይወቱን በደደቢት ቡድን ከተስፋው እስከ ዋናው ቡድን በመጫወት ሲያሳልፍ በማስከተል በወልዲያ እና ያለፉትን ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ በመጫወት ቆይቷል። ለሁለት ዓመት በጣና ሞገዶቹ ቤት ለመቆየት የተስማማው ተጫዋቹ የሕክምና ምርመራውን በማጠናቀቅ ፊርማውን ለማኖር ተቃርቧል።