ከፍተኛ ሊግ | አክሱም ከተማ ዋና አሰልጣኝ ቀጥሯል

አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃም ዳግም ወደ አክሱም ከተማ ተመልሷል።

በቀጣይ የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊጉ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ የሚገኙት አክሱም ከተማዎች የቀድሞ አሰልጣኛቸው ሲሳይ አብርሃምን በዋና አሰልጣኝነት ሾመዋል ፤ ባለፈው የውድድር ዓመት የትግራይ እግር ኳስ ፌደሬሽን ባዘጋጀው የክልል አቀፍ ውድድር በሀያ ስምንት ነጥቦች ስድስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ክለቡ ለቀጣይ የውድድር ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ የቀድሞ አሰልጣኙ ሲሳይ አብርሃምን በዋና አሰልጣኝነት ከቀጠረ በኋላ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ጀምሯል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከነቀምት ከተማ ጋር የተሳካ ጊዜ ያሳለፈው አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም ከሀያ ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ረዳት አሰልጣኝነት በተጨማሪ ሼር ኢትዮጵያ፣ አዳማ ከተማ፣ አክሱም ከተማ፣ ስሑል ሽረ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ ደሴ ከተማ እና ነቀምት ከተማ ማሰልጠኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከዓመታት በኋላ በ2017 የውድድር ዓመት ወደ ሀገራዊ ውድድር ለመመለስ በዝግጅት ላይ የሚገኙት አክሱም ከተማዎች ለማሰልጠን በመስማማት ፊርማውን አኑሯል።