የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ቦሌ ክፍለ ከተማ ወደ ዝውውሩ ገብቷል

ቦሌ ክፍለ ከተማ አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም የአስራ ሦስት ነባር ተጫዋቾችን እና የአሰልጣኙን ውል ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ መሪነት ላለፉት ዓመታት በሊጉ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻለው ቦሌ ክፍለ ከተማ ያለፈውን ዓመት 5ኛ ደረጃን በ48 ነጥቦች በመያዝ መቋጨት የቻለ ሲሆን ለቀጣዩ የውድድር ዘመንም የዋና አሰልጣኙን ኮንትራት ለአንድ ተጨማሪ ዓመት ያራዘመ ሲሆን አንድ አዲስ ተጫዋች እና የአስራ ሦስት ነባሮችን ውል ደግሞ ማደሱን ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ አመላክቷል።

ቡድኑን የተቀላቀለችው አዲሷ ፈራሚ የሸገር ከተማ አጥቂ ቅድስት ማቲዮስ ስትሆን ውላቸውን ያራዘሙት ደግሞ ግብ ጠባቂዋ ትብቃ ፈንቴ ፤ ተከላካዮች ፍቅርአዲስ ገዛኸኝ ፣ ቃልኪዳን ንቅበሸዋ ፣ እቴነሽ ደስታ ፣ ብዙነሽ ቡልቻ ፣ ቤተልሔም ስለሺ እና ፅግነሽ አዴ ፤ አማካዮች ሜላት አሊሙዝ ፣ ሚሊየን ጋይሞ እና ሜላት ጌታቸው  ፤ አጥቂዎች ፍሬሕይወት ተስፋዬ ፣ ጤናዬ ለታሞ እና ምርጥነሽ ዮሐንስ ናቸው።