ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተከላካይ ተማስፈረም ተስማምቷል

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ተከላካይ ለማስፈረም ተስማምቷል።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመሩት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በዝውውሩ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማምጣት እና የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ዝግጅት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በከተማው ዋንጫ ወደ ለፍፃሜው ጨዋታ ያለፈው ክለቡ አንድ ተከላካይ ለማስፈረም መስማማቱን አውቀናል።

ተጫዋቹ አብዱላሂ አላዩ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ሊግ ሲጫወት የነበረው ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኦሮሚያ ፖሊስ ጥሩ ጊዜን አሳልፏል። ተከላካይ ሆኖ ጎሎችን በማስቆጠር የሚታወቀው ተጫዋቹ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ መድንን ሲያሸንፍ የማሸነፊያ ጎል ማስቆጠሩ ይታወቃል። የህክምና ምርመራውን ያደረገው ተጫዋቹ ነገ በይፋ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።