መቐለ 70 እንደርታ አማካዩን ለማስፈረም ተስማምቷል

ምዓም አናብስት ጋናዊውን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።

ቀደም ብለው ግዙፉን ጋናዊ አጥቂ ኮፊ ኮርድዚ ያስፈረሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ ሌላኛውን ጋናዊ የአማካይ ተከላካይ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ደግሞ የሃያ ስምንት ዓመቱ ቤንጃሚን አፉቱ ነው።

በ2017 በካሬላ ዩናይትድ የእግር ኳስ ሕይወቱ የጀመረው እና በጋና ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ለሆነው ኸርትስ ኦፍ ኦክ እና ለግብፁ ክለብ ኢስተርን ካምፓኒ መጫወት የቻለው ይህ የተከላካይ አማካይ በ2021 ከጋናው ታላቅ ክለብ ጋር  የፕሪሚየር ሊግ እና የጋና ኤፍኤ ዋንጫን ያሸነፈ ሲሆን በወቅቱም ከሊጉ ምርጥ የተከላካይ አማካዮች ተርታ ተመድቦ ነበር። በጋና እና በግብፅ ክለቦች ከተጫወተ በኋላ ላለፉት ዓመታት በሳውዲ አረብያው ክለብ አል ታቃዶም ቆይታ የነበረው ጋናዊው ከአል ቃሲሙ ክለብ ጋር የነበረው ውል መገባደዱን ተከትሎ ማረፍያውን መቐለ 70 እንደርታ ለማድረግ ከስምምነት ደርሷል።