የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ውድድር ለሚያደርገው ዝግጅት ለ38 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጓል።
በታንዛንያ አስተናጋጅነት በሚካሄው ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣርያ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ሹመት ቀደም ብሎ ሲደረግ በዋና አሰልጣኝነት ሥዩም ከበደ ፣ በረዳት አሰልጣኝነት ደግሞ ዐቢይ ካሣሁን እና አምሳሉ እስመለዓለም ሆነው የተሾሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት 38 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።
ግብ ጠባቂዎች
አብዩ ካሳዬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ አማኑኤል ደስታ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ታምራት ቅባቱ (መቻል)፣ እንደሻው ኡርጋ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አብነት ሀብቴ (ወላይታ ድቻ)
ተከላካዮች
አብዱልሰመድ ዩሱፍ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ኪሩቤል ዳኜ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ እስራኤል ሠማያት (ሀዋሳ ከተማ)፣ ድልአዲስ ገብሬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ፍፁም ፍትሕአለው (ባህር ዳር ከተማ)፣ ዋንጫ ቱት (ኢትዮጵያ መድን)፣ ቢኒያም በቀለ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ብሩክ ታረቀኝ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አበበ ሸኖ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ዮናስ ለገሠ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ተመስገን ታደሰ (ኢትዮጵያ ቡና)
አማካዮች
ሚኪያስ ፀጋዬ (ኢትዮጵያ ቡና)፥ ሚራጅ ሰፋ (ወልዋሎ)፣ ያሬድ ብሩክ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዣቪር ሙሉ (ፋሲል ከነማ)፣ አንዋር በድሩ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ መላኩ አየለ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ቃለአብ ፈለቀ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ዮሐንስ መንግሥቱ (መቻል)፣ ሚኪያስ በዳሶ (አዳማ ከተማ)፣ ቴዎድሮስ ባንቴ (አርባምንጭ ከተማ)፣ ሰሎሞን ባንቴ (ወልዋሎ)
አጥቂዎች
ቸርነት መንግሥቱ (ወላይታ ድቻ)፣ ፀጋ ከድር (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አብነት ዓባይነህ (አርባምንጭ ከተማ)፣ የአብስራ ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ዮናታን ኤልያስ (ወላይታ ድቻ)፣ ዳግም አወቀ (ፋሲል ከነማ)፣ ዳዊት ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ አንተነህ ተፈራ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሄኖክ ኤርሚያስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ሀብታሙ ጉልላት (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሚልዮን ኃይሌ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከነገ መስከረም 7 ጀምሮ በካሌብ ሆቴል በመሰባሰብ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩ ይሆናል።