የ2005 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒየን የነበሩት ሰማያዊዎቹ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥረዋል።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከ2002 ጀምሮ እስከ 2010 ድረስ ሲሳተፍ ቶይቶ ወደ ታችኛው የሊግ ዕርከን ለመውረድ የተገደደው የ2005 የሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን ቻምፒዮን የነበረው ደደቢት ከዓመታት በኋላ በከፍተኛ ሊጉ ላይ እንዲሳተፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ያስተላለፈውን መመሪያ ተንተርሶ በ2017 የውድድር ዘመን ላይ የሚካፈል ሲሆን ለዚህም ይረዳው ዘንድ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥርን ፈፅሟል።
የቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት አሰልጣኝ መሳይ በየነ ናቸው። የጅማ ከተማ ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፣ የኢትዮጵያ መድን ረዳት አሰልጣኝ ፣ የነቀምት እና ዱከም ከተማ እንዲሁም የፌዴራል ፓሊስ አሰልጣኝ ሆነው የሠሩት አሰልጣኝ መሳይ በሁለት አጋጣሚዎች ቡታጂራ ከተማን ያሰለጠኑ ሲሆን በቡራዩ ከተማ ከነበራቸው ቆይታ በኋላ ቀጣይ ክለባቸው ደደቢት ሆኗል።