አራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች አህጉራዊ ጨዋታ ለመምራት ወደ አልጀርያ ያቀናሉ።
አራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ እንደሚመሩ ታውቋል። በቀጣይ ዓርብ የአልጀርያው ቤሎዚዳድ ከ ቡርኪናፋሶው ዶዋንስ የሚያካሂዱትን የሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ አራት ኢንተርናሽናል ዳኞች ማለትም ቴዎድሮስ ምትኩ በዋና ዳኝነት ፋሲካ የኋላሸት እና ትግል ግዛው በረዳትነት እንዲሁም ኃይለኢየሱስ ባዘዘው በአራተኛ ዳኝነት ጨዋታውን ለመምራት የተመደቡ ሲሆን በዛሬው ዕለት ወደ አልጀርያ ያመራሉ።
በስታደ ማማዱ ኮናቴ በተካሄደው የመጀመርያ ዙር ጨዋታ አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት የተሸነፉት ቤሎዚዳዶች ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍ በመጪው ዓርብ በሜዳቸው ሚሎድ ሀደፊ ስቴድየም የሚያካሂዱትን ተጠባቂ ጨዋታ ኢትዮጵያውያኖች ይመሩታል።