ወልዋሎዎች ተጨማሪ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማምተዋል

ባለፉት የውድድር ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ቢጫዎቹ ለማምራት ተስማምቷል።


ቀደም ብለው አጥቂው ዳዋ ሆቴሳን ያስፈረሙት በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ተጨማሪ የማጥቃት ባህሪ ያለው ተጫዋች ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሰዋል። ቡድኑን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ተጫዋች ደግሞ የመስመር ተጫዋቹ ቡልቻ ሹራ ነው።

ከአዳማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በ2007 ላይ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ እስከ 2012 ድረስ አሳዳጊ ክለቡን በማገልገል ባለፉት ዓመታት በሰበታ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና በመጫወት የቆየው ይህ ተጫዋች ከክለቡ ጋር የነበረውን ውል ማገባደዱን ተከትሎ መዳረሻውን ወልዋሎ ለማድረግ ከስምምነት ደርሷል።