የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ጉዞውን ዛሬ ሲጀምር የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭትን በተመለከተ ተከታዩን መረጃ ይዘናል።
የ2017 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም በሁለት መርሐግብሮች የሚጀመር ሲሆን የሊጉ ጨዋታዎችም የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ያገኛሉ ወይስ አያገኙም በሚል በርካቶች ጥያቄ ሲያነሱ ይስተዋላል። በሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት እየተደረገበት ላለፉት አራት ዓመታት ቆይታን ያደረገው ፕሪሚየር ሊጉ በተቀመጠው የውል ዘመን መሠረት የአክሲዮን ማኅበሩ እና የሱፐር ስፖርት ስምምነት አምስተኛ እና የመጨረሻ ዓመቱ ላይ የደረሰ ሲሆን ምንአልባት በዚህ ዓመት በርካታ ጨዋታዎች ሽፋን ላያገኙ እንደሚችሉ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ዛሬ መቐለ 70 እንደርታ ከ ሀዲያ ሆሳዕና ፣ አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ መተላለፉን የሚጀምረው የሱፐር ስፖርት ቀጥታ ስርጭት እስከ አሁን ባለው መረጃ የሁለት ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች እንደሚያስተላልፍ ሲጠበቅ ነገር ግን በቀጣይ የሦስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይተላለፉ እንደሚችሉ ተሰምቷል።