የወልዋሎ አምበሎች እነ ማን ይሆኑ?

የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ አምበሎች ታውቀዋል።

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት እና ራሳቸውን ለማጠናከር በርከት ያሉ ዝውውሮችን በመፈፀም የውድድሩን መጀመር በመጠባበቅ ላይ የሚገኙት ቢጫዎቹ አምበሎች ታውቀዋል። በዚህ መሰረት ዳግም አሳዳጊ ቡድኑን ለማገልገል ቡድኑን የተቀላቀለው እና ባለፈው የውድድር ዓመት ቡናማዎቹን በአምበልነት ያገለገለው ግብ ጠባቂው በረከት አማረ፣ የቡድኑን የፊት መስመር ይመራል ተብሎ የሚጠበቀው አጥቂው ዳዋ ሆቴሳ፣ ከድሬዳዋ ከተማ ቡድኑን የተቀላቀለው የመሀል ተከላካዩ እያሱ ለገሰ እና የግራ መስመር ተጫዋቹ ጋዲሳ መብራቴ የቡድኑ አምበሎች ሆነው ተመርጠዋል።

በቅድመ ውድድር ወቅት በርከት ያሉ ጨዋታዎች ያከናወኑት ወልዋሎዎች የፊታችን ቅዳሜ ባህር ዳር ከተማን በመግጠም ውድድራቸውን ይጀምራሉ።