በአሰልጣኝ ኢዮብ ተዋበ የሚመሩት ድሬዳዋ ከተማዎች የአስራ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲያጠናቅቁ የሦስት ነባሮችን ውል ደግሞ አራዝመዋል።
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ላይ በተከታታይ ዓመታት እየተሳተፉ የሚገኙት ድሬዳዋ ከተማዎች የተጠናቀቀውን ዓመት በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በሰበሰቧቸው 21 ነጥቦች 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ማጠናቀቅ የቻሉ ሲሆን ለዘንድሮው የውድድር ዘመንም በአሰልጣኝ ኢዮብ ተዋበ እየተመሩ በፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ይረዳቸው ዘንድ በዝውውሩ አስራ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የሦስት ነባሮችን ውል ደግሞ አራዝመዋል።
ግብ ጠባቂዋ ሒሩት ደሴ በመቻል እና ሲዳማ ቡና ከነበራት ቆይታ በኋላ ወደ ቀድሞው ክለቧ ስትመለስ ፣ ሮማን አምባዬ ግብ ጠባቂ ከቦሌ ፤ የቀድሞዋ የሲዳማ ፣ መቐለ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ያለፈውን ዓመት በአዲስ አበባ ቆይታ የነበራት አጥቂዋ ዮርዳኖስ ምዑዝ ፣ በሀዋሳ እና ኤሌክትሪክ የምናውቃት የተከላካይ አማካዩዋ እታለም አመኑ ዳግም ወደ ቀድሞው ክለቧ ስትመለስ ፣ በንግድ ባንክ ኤሌክትሪክ እና ባህርዳር የተጫወተችው የመስመር ተከላካዩዋ ብዙነሽ ሲሳይ ፣ በኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ በመቀጠልም በቦሌ እና አዲስ አበባ የተጫወተችው የግራ ተከላካዩዋ የምስራች ሞገስን ጨምሮ ማህሌት ወርቁ ተከላካይ ከይርጋጨፌ ቡና ፣ ስመኝ ተስፋዬ አማካይ ከአዳማ ፣ ማንዐየሽ ተስፋዬ አማካይ ከልደታ ፣ ይዲዲያ አጫ አማካይ ከቦሌ ፣ አለሚቱ ድሪባ አጥቂ ከልደታ እና በከፍተኛ ሊጉ የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ የነበረችው ቤቴልሔም ሽመልስ ከፋሲል ቡድኑን ተቀላቅለዋል።
ቡድኑ የዐይናለም ይድነቃቸው ፣ ሰርካዲስ ጉታ እና አያን ሙሳን ኮንትራት ደግሞ አራዝሟል።