የኢትዮ ኤሌክትሪክ አምበሎች ታውቀዋል

ከአንድ ዓመት በኋላ ዳግም ወደ ሊጉ የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቡድኑን የሚመሩ አምበሎችን አሳውቋል።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመሩ ለዘንድሮ የውድድር ዓመት ቡድናቸውን ለማጠናከር ሽመክት ጉግሳ ፣ ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ፣ ሐብታሙ ሸዋለም፣ ፍቃዱ አለሙን ፣ በፍቃዱ አስረሳኸኝ፣ እዮብ ገብረማርያም፣ አሸናፊ ጥሩነህ እንዲሁም ሌሎች ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ሲቀላቅሉ የወሳኝ ነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘማቸው ይታወሳል።

ዝግጅታቸው በቢሸፍቱ ከተማ ሲዘጋጁ የቆዮት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቡድኑ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለፍፃሜ ደርሰው የነበረ ሲሆን አሁን ለዋናው የሊጉ ውድድር ወደ ድሬደዋ ጉዞ ጀምረዋል።

ቡድኑ በቀጣዮቹ የሊጉ ውድድር እንዲመሩ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ አንበሎቻቸው እነማን እንደሆኑ ሲያሳውቁ በዚህም መሠረት ባለብዙ ልምዱ ሽመክት ጉግሳ ቁጥር አንድ ተመራጫቸው ሲሆን ቡድኑ በከፍተኛ ሊግ ተሳትፎ አንበል የነበረው ጌቱ ባፋ የኤልፓዎች ሁለተኛ አንበል ሆኖ ተመርጧል።