የ2017 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ከመቼ ጀምሮ እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚደረገው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2017 የውድድር ዘመን የሚጀመርበት ቀን መቼ እንደሆነ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል። አስራ አራት ክለቦችን ተፎካካሪ የሚያደርገው የዕንስቶች ውድድር በቀጣዩ ወር ጥቅምት 24 በይፋ ጅምሩን እንደሚያደርግ ታውቋል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለተከታታይ የውድድር ዘመናት አሸናፊ እያደረገ የነበረው ይህ ውድድር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ መቻል ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ አርባምንጭ ከተማ ፣ ሀምበርቾ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ አዳማ ከተማ ፣  ልደታ ክ/ከተማ እና አዲስ አዳጊዎቹ ባህር ዳር ከተማ እና ቂርቆስ ክ/ከተማ የሚሳተፉበት ይሆናል።