የጣና ሞገዶቹ አምበሎቻቸውን አሳውቀዋል

በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማን በአምበልነት የሚመሩ ተጫዋቾችን ክለቡ አሳውቆናል።

በዛሬው ዕለት የ2017 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሰቲ ጋር በማድረግ የሚጀምሩት የጣና ሞገዶቹ በውድድር ዓመቱ አምበል አድርገው የሾሟቸውን ተጫዋቾች አሳውቀውናል።

በዚህም የቀድሞው ሀላባ ከተማ ፣ ሙገር ሲሚንቶ ፣ ሃዋሳ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ መቻል ፣ ሲዳማ ቡና ተጫዋች እና ባሳለፍነው ዓመት ደግሞ ወደ ባህር ዳር ከተማ ያቀናው ፍሬው ሰለሞን በሁለተኛ ዓመት ቆይታው የክለቡ አምበል ሆኖ ሲመረጥ የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዲያ ሆሳዕና ተጫዋች ፍሬዘር ካሳ እንደ ፍሬው ሁሉ በሁለተኛ ዓመት የባህር ዳር ከተማ ቆይታው የቡድኑ ሁለተኛ አምበል ሆኖ ተሰይሟል።