ሠራተኞቹ ተጠቃለው ድሬዳዋ አልገቡም

የ2017 የውድድር ዘመን ዛሬ የመጀመርያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ወልቂጤ ከተማዎች አሁናዊ ሁኔታ………..

ባለፈው የውድድር ዓመት በብዙ ውስጣዊ ችግሮች ተፈትነው ለዘንድሮው በሊጉ መቆየታቸውን ያረጋገጡት ወልቂጤ ከተማዎች አሁንም ከችግራቸው ሙሉ ለሙሉ ሳይላቀቁ የውድድር ዓመቱን ሊጀምሩ ይመስላል።

ቡድኑ በሀዋሳ ከተማ ለሳምንታት ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቶ ውድድሩ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ ቀድሞ ይደርሳል ቢባልም የሆነው ግን ሌላ ነው ፤ ሶከር ኢትዮጵያ እንዳኘችው መረጃ ከሆኑ ቡድኑ እስካሁን ድረስ ተጠቃሎ ድሬዳዋ ከተማ እንዳልገባ ለማወቅ ተችሏል።

በትናንት ዕለት ገሚሱ የቡድኑ አባላት ድሬደዋ መድረሳቸው ሲታወቅ ዋና አሰልጣኙን ጨምሮ የቀሩት የቡድኑ አባላት ግን ይህን ዘገባ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የሚገኙ ሲሆኑ ረፋድ ላይ ድሬደዋ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሠራተኞቹ የሊጉ የመጀመርያ ጨዋታቸውን ዛሬ አስር ሰዓት ላይ ከመቻል ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።