የጦና ንቦቹ አምበሎች ተለይተዋል

በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች ሦስት አምበሎቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2017 የውድድር ዘመናቸውን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በዛሬው ዕለት በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀምሩት ወላይታ ድቻዎች በክረምቱ ከአምናው አንፃር የተሻሉ ዝውውሮችን የፈፁበትን ጊዜ አሳልፈዋል።

ቡድኑም ድሬዳዋ ከደረሰ በኋላ በ2017 በአምበልነት የሚመሩትን ተጫዋቾች መርጦ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል ፤ በዚህም መሠረት ከወጣት ቡድኑ ተገኝቶ ላለፉት አራት ዓመታቶች የቡድኑ ተቀዳሚ የግብ ዘብ ሆኖ በማገልገል ላይ የማገኘው ቢኒያም ገነቱ የመጀመሪያ አምበል ሆኖ ተመርጧል።

በተጨማሪነትም ወደ ቀድሞው ክለቡ ተመልሶ ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው አጥቂው ባዬ ገዛኸኝ እና ቁመታሙ የመሐል አማካይ አብነት ደምሴ በቅድመ ተከትል በአምበልነት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።