እያሱ ታምሩ የቀድሞ ክለቡን ተቀላቅሏል

የአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬው ኢትዮጵያ ቡና የመስመር አጥቂ እና ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን ዳግም አግኝቷል።

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታቸውን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለበት የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት ለማረፍ የተገደዱት ኢትዮጵያ ቡናዎች የፊታችን ዓርብ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ከሚያደርጉት የሁለተኛ ሳምነት ጨዋታ በፊት የቀድሞው ተጫዋቻቸውን የግላቸው አድርገዋል።

ወደ ቀደሞ ቡድኑ የተመለሰው የመስመር አጥቂው እና ተከላካዩ እያሱ ታምሩ ነው ፤ ከወሊሶ መነሻውን ካደረገ በኋላ ለሀላባ ከተማ ሲጫወት ባሳየው ድንቅ ብቃት ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቅሎ ከፕሪምየር ሊጉ ጋር መተዋወቅ የቻለው ተጫዋቹ ወደ ሀድያ ሆሳዕና በማምራት ሁለት ዓመት ቆይታን ካደረገ በኋላ ያለ ክለብ ቆይቶ በዛሬው ዕለት በድጋሚ ቡናማዎቹን ተቀላቅሏል።