ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ቡናማዎቹ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ቋጭተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታቸው በይደር የቆየላቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች በአሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ እየተመሩ በሁለተኛው ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክን በመግጠም ዓመቱን ይጀምራሉ። በትላንትናው ዕለት የቀድሞ ተጫዋቻቸውኢያሱ ታምሩን የግላቸው ያደረጉት ቡናማዎቹ በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።

ረጂብ ሚፍታህ የቡድኑ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል። በኮልፌ ቀራኒዮ እና ቤንች ማጂ ቡና የከፍተኛ ሊግ ቆይታ የነበረው እና ያለፈውን ዓመት ደግሞ ከባህር ዳር ከተማ ጋር በፕሪምየር ሊጉ ያሳለፈው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ እና በአሜሪካን ሀገር ከነበረው የዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ጨዋታዎች በኋላ በ2015 ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በፋሲል ከነማ ተጫውቶ የነበረው አጥቂው ኪሩቤል ደሳለኝ ከአንድ ዓመት በኋላ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቅሏል።