ከፍተኛ ሊግ | ሻሸመኔ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

በመጡበት ዓመት ከፕሪምየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረዱት ሻሸመኔ ከተማዎች አዲስ አሰልጣኝ ቀጥረዋል።

በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተካፋይ የነበሩት ሻሸመኔ ከተማዎች ዳግም ወደ ሊጉ ለመመለስ በማለም በዘንድሮው የከፍተኛ ሊግ ጉዟቸውን ለመጀመር ከወራት በፊት የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥርን ለመፈፀም ማስታወቂያን ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ክለቡም ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመራው እስማኤል አቡበከርን ስለመምረጡ ማረጋገጥ ችለናል።

ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማሳደግ የቻለው እና በተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ ክለቡን በፕሪምየር ሊጉ የመራው አሰልጣኝ እስማኤል በኮልፌ ቀራኒዮ እንዲሁም በተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ደግሞ ከሀላባ ከተማ ጋር ቆይታን አድርጎ ወደ ሻሸመኔ አምርቷል።