ምዓም አናብስት የአንድ ተጫዋች ዝውውር አገባደዋል

በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመሩት መቐለ 70 እንደርታዎች የመስመር ተጫዋቹን ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል ተስማምተዋል


በውድድር ዓመቱ የመጀመርያ ድላቸውን በማስመዝገብ ነጥባቸውን አራት ማድረስ የቻሉት እና በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመሩት መቐለ 70 እንደርታዎች የመስመር ተጫዋቹን አስፈርመዋል ፤ ቡድኑን ለመቀላቀል ዛሬ ጠዋት ፌርማውን ያኖረው ተጫዋች ደግሞ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በኢትዮጵያ መድን ቆይታ የነበረው ብሩክ ሙልጌታ ነው።

ከዚህ ቀደም በኮልፌ ቀራንዬ፣ ሲዳማ ቡና የመጨረሻዎቹ ሁለት የውድድር ዓመታት ደግሞ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ባለፈው የውድድር ዓመት በሀያ ስምንት ጨዋታዎች ተሰልፎ 1961 ደቂቃዎች ቡድኑን አገልግሏል።


ቅዱስ ጊዮርጊስን ካሸነፉ በኋላ ለተጫዋቾቻቸው የቀናት ዕረፍት የሰጡት አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ በቀጣይ ሦስት ቀናት ወደ ልምምድ እንደሚመለሱም ታውቋል። 

ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በተያያዘ ሌላ ዜና በጉዳት ምክንያት የመጨረሻው ጨዋታ ያመለጣቸው ተከላካዩ መናፍ ዐወል እና አማካዩ የዓብስራ ተስፋዬ ውድድሩ ከሀገራት ዕረፍት ሲመለስ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።