ፈረሰኞቹ የፊት መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ተስማምተዋል።
ቀድም ብለው አፈወርቅ ኃይሉን የግላቸውን ለማድረግ የተስማሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አሁን ደግሞ ኮትዴቭዋራዊውን አጥቂ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል። ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ደግሞ የሀያ ሁለት ዓመቱ ተጫዋች መሐመድ ላሚን ኮኔ ነው።
አንድ ሜትር ከዘጠና የሚረዝመው ግዙፉ አጥቂ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሀገሩ ክለብ ኤስክ ሜሞሴስ ቆይታ ያደረገ ሲሆን አሁን ደግሞ ፈረሰኞቹን ለመቀላቀል መስማማቱን ተከትሎ በነገው ዕለት ኢትዮጵያ ይገባል።